የሰሚውና
የአሰሚው አልተገናኝቶ
ከሰሚው ልጀምር፡፡በዚህ ዘመን ራሴን ጨምሮ እውነቱን የሚነግሩንን፣ችግሮቻችንን የሚያሳዩንንና፣የሚገሥጹንን
ሰዎች በፍጹም አንሻም፡፡ነገር ግን የሚክቡንንና ከፍ ከፍ የሚያደርጉንን ሰዎች ነፍሳችን አጥብቃ ትፈልጋለች፡፡ይህ አግጦ የወጣ ችግራችን ነው፡፡
“የእግዚብሔር ቃል ስለዚሁ ችግር ሲገልጽ “ሕይወት የሚገኝበትን
ትምህርት የማይታገሡበት ዘመን ይመጣልና፤ነገር ግን ጆሮቻቸውን የሚያሳክክ ስለ ሆነ እንደ ገዛ ምኞታቸው ለራሳቸው አስተማሪዎችን
ያከማቻሉ፡፡እውነትን ከመስማት ጆሮቻቸውን ይመልሳሉ……” (2 ጢሞቲዎስ 4፡3-4) ብሏል፡፡በቅንነት ራሳችንን በእግዚአብሔር
ብርሃን ብንፈትሽ፣ትምህርቶችን የምንሰማው መርጠን ነው፡፡አስተማሪዎችን የምንመርጠው “ከሙዳችን ጋር” የሚሄዱትን አስበን ነው፡፡እንዳውም
የሕይወት ምልልሳችን አስጠልቶ እየታየ “ተመለስ” ስንባልስ
መቼ እሺ እንላለን? በጭራሽ፣በፍጹም፡፡ይህ የመጀመሪያው ችግራችን መሆኑ ነው፡፡
የአሰሚውን ችግር ደግሞ እነሆ፡፡ዛሬ ዛሬ ተግሣጽ ያለው ትምህርት እምብዛም አይሰማም፤ “ይሳካላችኋል” ወይም “ትሻገራላችሁ” የሚል መልእክት ነው በአብዛኛው ከመድረክ የሚስተጋባው፤ዝማሬውም እንዲሁ፡፡ወገኖቼ በዚህ አካሄዳችን
እየተሳካልን ይመስላችኋል? አይመስለኝም፡፡ቃሉ እንደሚነግረን፣በኤርምያስ ዘመን የነበሩ ጥበበኞችና አስተማሪዎችን ስናይ ራስ ወዳዶችና
ስስታሞች ነበሩ፡፡ታዲያ መንጋው እንዳይከዳቸው፣የሚያባብል ትምህርት እንጂ ሙሉ ፈውስን የሚያመጣና ከጥፋት የሚመልስ ትምህርት አያመጡም
ነበር፤የእግዚአብሔር ቃል እንዲህ ብሏቸዋልና፡-
ጌታ እግዚአብሔር ምዕመኑ ላይ ያገጠጡና መታከም የሚገባው ብዙ ችግሮች እያሉት “ሰላም ነው” በሚሉ አገልጋዮች ማዘኑ ምን ጥርጥር አለው? እንዲህ ያለውን አካሄድና አሠራር “አስጸያፊ” ብሎም
በዚሁ በጠቀስሁት ቃል ላይ ፈርጆታል፡፡
እናም ወገኖቼ ዋነው መልእክቴ እንዲህ ነው፡-የእግዚአብሔር ቃል “ምሕረትና እውነት ተገናኙ፤ጽድቅና ሰላም ተስማሙ”(መዝሙር
84፡10)እንደሚለው መለኮታዊ ግጥጥሞሽ፣ሰሚና አሰሚ በጌታ የቃል መርሕ እንዲገናኙ እንጸልይ!
No comments:
Post a Comment