Friday, August 30, 2013

ከልብህ ኀዘንን አርቅ

ከልብህ ኀዘንን አርቅ


ወደ ስምንት አመት ገደማ ይሆናል፡፡በአንድ ከፍ ያለ የልብ ስብራት ውስጥ ሆኜ መቆዘም አብዝቼ ነበር፡፡ኀዘኔ ከበድ ያለ ስለነበር ከሰው ጋር መገናኘትና ማውራት አስጠልቶኝ ሁሉ ነበር፡፡በዛ ሁኔታ ውስጥ ሳለሁ የጌታ መንፈስ ደረሰልኝና አንድ ነገር አበራልኝ፡፡እርሱም ይህንን ያለሁበትን ሁኔታ የማራገፍ ኀላፊነት የኔ እንደሆነ በቃሉ ብርሃን ተገነዝብኩ፡፡ ውስጤን የለወጠው ቃል የሚገኘው መክብብ ላይ ሲሆን እንዲህ ይላል፡-


“ከልብህ ኀዘንን አርቅ”(መክብብ 11:10)


ይህ ቃል የበራልኝ ቀን በሚገርም ሁኔታ ነበር ውስጤ በግርምት የተሞላው፡፡አዝኜ የሰይጣንና የአጋንንቱ መጫወቻ ሆኜ እያላዘንሁ መቀመጥ እንደሌለብኝ በሚገባ ገባኝ፡፡ጌታ ከዛም ከነበርሁበት ሁኔታ ለመውጣት  ጠንከር ያሉ ጸሎቶችን በመያዝ ትግል መጀመር እንዳለብኝ አመለከተኝ፡፡


ባጋጣሚ የምኖርበት ቤት አጠገብ አንድ የመሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ቤ/ክ ነበርና እዚያ በፈረቃ ግቢውን የሚጠብቁትን ሠራተኞች እያስፈቀድሁ ለረጅም ሰዓታት ባዶ አዳራሽ ውስጥ መጮኽ ጀመርሁ፡፡መጀመሪያ ይህንን ትግል ስጀምር ልክ ግምብ የመግፋት ያህል ይሰማኝ ነበር፡፡የሚሰማኝ ስሜት ሳይበግረኝ በጸሎት መገሥገሥ ጀመርሁ፡፡በመሀል በመሀል አንዳንዴ ካለሁበት ሁኔታ ጋር የሚዛመድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያጠናሁና እያሰላሰልሁ ከዚያ ደግሞ ቀጥዬ በመቃተትና የጌታ መንፈስ እንዲረዳኝ በመማጸን ሳልፈወስ ከምሽጌ ላልወጣ ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡


ለተወሰኑ ቀናት እንዲህ ባለ ሁኔታ  ካሳለፍኩ በኋላ ሁኔታው ሁሉ ተገልብጦ ሰላምና ደስታ በማያቋርጥ ሁኔታ በልቤ ውስጥ ይፈስ ጀመር፡፡ዝማሬ፣ አምልኮ፣ስግደት ፣ውዳሴ ወዘተ በሕይወቴ ተትረፈረፈ፡፡እየጸለይኩ ውዬ፤ስለጌታ አውርቼ ፤አመስግኜ ወዘተ አልረካም ነበር፡፡እዚህ ምድር ላይ ሁሉ የምኖር አልመስለኝ ሁሉ አለ፡፡የእግዚአብሔር ህልውና በሚገርም ሁኔታ እላዬ ላይ ነበር፡፡ብቻዬን ሆኜ ማንም ሳያወራኝ ሁሉ ሳቅ ያስፈነድቀኝ እንደነበር ሁሉ ትዝ ይለኛል፡፡የነበርኩበትን ሁኔታ በቃላት መግለጽ ያዳግተኛል፡፡ወገኖቼ ልብ በሉ እያጋነንሁ አይደለም እውነተኛ ነገር ነው የምናገረው፡፡ክርስትና ዝም ብሎ ስርአት እንዳልሆነ በሕይወቴ አይቻለሁ፡፡


“እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ” (ኢሳ 35፡10) ብሎ የሚለው ቃል ምን ማለት እንደ ሆነ በጥቂቱም ቢሆን ይገባኛል::አዎ ያ ሁሉ ኀዘንና ትካዜ የት አንደገባ እስገሚገርመኝ ድረስ በሐሤት ተጥለቀለቅሁ፡፡ለዚህ ነው ቃሉ “በዚያም ቀን ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ይወርዳል ቀንበሩም ከውፍረት የተነሳ ይሰበራል”(ኢሳ 10፡27) የሚለው፡፡ማለትም ጠበቅ  ያሉ ጸሎቶችን ስናዘወትር የጌታ መንፈስ በውስጣችን እየጨመረ ስለሚሄድ ማንኛውንም አዚም ለመስበር የምንችልበትን አቅምና ጉልበት እናገኛለን፡፡


በጽኑነት ከልብ ሆነንና በቀጣይነት ሳንታክት በምንጸልየው ጸሎት ብዙ ድንቅ መለኮታዊ ነገሮችን እናያለን የሚል መረዳት አለኝ ፡፡ስለዚህ ከነካ ነካ የጸሎት ሕይወት ጌታ ወደ ጠለቀ ልምምድ እንዲከተን ሳንታክት ፊቱን እንሻ፡፡እንዲህ ብናደርግ ያስደንቀናል፡፡ስሙ ለዘላለም የተባረከ ይሁን!

Thursday, August 29, 2013

እውነተኛ ውስጣዊ ደስታ

HOW TO HAVE REAL JOY

There are lots of ideas floating around out there as to how a person can truly be happy, yet the answer is right within us, if we are Christians.

Christ lists nine ways in Matthew 5:1-12 that we can be happy. These ways include being pure in heart, being humble, being gentle, being peacemakers, hungering for righteousness, being merciful, and having an eternal perspective about life. And let us not forget that we are to have joy when we are persecuted and suffer for righteousness’ sake and for Jesus’ sake. Christ’s message to us is that joy is possible at all times and in all areas of life, if we live as He is commanding us to live. Those who were listening to this discourse at the time were hoping that Christ would conquer
Rome and set up a Jewish empire.  They wanted their circumstances changed so that they could be happy.  Yet Christ gave up His life, He did not fix their circumstances, and He did not set up an earthly kingdom.  Still He said that they could be happy, if and only if they let the kingdom of Christ rule in their hearts.  The happiness that Christ was referring to was clearly not circumstantial in nature.  Rather, it was all about investing in heavenly priorities and putting faith in Christ regardless of the circumstances.  In Christ alone, we can find fullness of joy.  As Psalm 16:11 says, “In His presence is fullness of joy.” Jesus alone can make us happy. 
The believer’s joy is not a fleshly, conjured up type of smiling, niceness, and politeness no matter what. Such is fake and worldly. What Christ is after is a happiness that stems from hope in a Person, even if our face is downcast, even when tears fall, and even when we are in great pain. Joy is an issue of the heart, and it gives us strength in our inner person to carry on in obedience and faithfulness. As Nehemiah 8:10 says, “Do not be grieved, for the joy of the LORD is your strength.”  True joy transcends circumstances such that, even when we are suffering, we can have joy in our hearts. We may feel pain in the members of our bodies, but we can have joy in our spirits and in our hearts. We may be mocked, ridiculed, persecuted, and harassed, yet we can be happy because we are always in the presence of God. There is nothing like knowing that our joy remains full even when we have been rendered empty of all that we had thought we needed to sustain our happiness.

Yet even Christians sometimes fail to experience joy in both good times and bad. Sometimes we get so caught up in the issues of life that we forget to rejoice in the Lord. Rejoicing in the Lord is a choice. This is why Paul commanded us twice in Philippians 4:4 to rejoice in the Lord always. Just because we are in the presence of God (seeing that He indwells our hearts) does not mean that we necessarily will experience joy unless we by faith rest in Him. We must make a choice to let Christ be our joy, to let Him give us joy, and to believe that He will do just that. If we falter in our faith, we will try to manufacture our own joy, which will not last and will fail. Only when we find our happiness in the person of Jesus as we rest in Him can we experience true joy.  We must rest in Him, love Him, enjoy Him, worship Him, and trust in the fact that our lives are indeed hidden with Christ in God (Colossians 3:3).  Constant communion with God is possible through Christ Who works in and through us. 

John 15:11 says, “These things I have spoken to you so that My joy may be in you, and that your joy may be made full.” John reminds us that we will not have fullness of joy unless we abide in Christ which involves keeping His commands and putting our full trust and confidence in Him.  Obedience to God is central to experiencing the joy of God. If we do not follow His will and listen to the Holy Spirit in accordance with God’s Word, we will lose out on our joy. There may be some there, seeing that we will still know that we are saved, yet the fullness of joy will be gone because we are not being and doing what God would have us be and do. The darkest times of life are the times of disobedience because there is a lack of joy even if circumstances are easy.  In fact, the brightest and most joyous times can actually be when we triumph in faith and obedience during the most difficult and oppressive of times.  If we want joy that is supernatural and truly divine, then we must walk in obedience, resting in God all the while. 

Sin’s pleasures are temporary (Hebrews
11:25), but God’s joy endures forever.  When we put our confidence in God and choose to have His joy, we can have access to a fruit of the Spirit which is unspeakably wonderful. It transcends the issues of life and draws our minds to heaven. His joy is a pleasure that is forever, and we can experience it even this very moment if we walk in faith and obedience.Taken from Relevant Bible Teaching

እውነተኛ ከውስጥ የሆነ መንፈሳዊ ደስታ ውስጥ ለመግባት ከፈለግህ የሚከተሉት ለማድረግ ጨክን፡-

  • ማንኛውንም የሰራሀቸውን ሀጢያቶች በሚገባ ተናዘዝ

  • ብቅ እያሉ የሚያስቸግሩህን ሀጢያቶች  በመንፈስ ግደል

  • የእግዚአብሄርን ቃል ባልተከፋፈለ ልብ ጊዜ ሰጥተህ አጥና አሰላስል

  • አጥብቀህ ከልብ ሳታሰልስ ጸልይ

  • እራስህን ከመስማት ይልቅ እምነትህን በሚያጠነክሩ ቃሎችና ሀሳቦች እራስን መስበክን ተለማመድ

  • ትእግስተኛ ለመሆን ጣር

  • በአግባቡ ምግብህን ተመገብ

  • በቂ አካላዊ እንቅስቃሴ አድርግ

እነዚህን ብታደርግ አእምሮን የሚያልፍ ደስታ ውስጥ እራስህን ታገኘዋለህ!

መንፈሳዊ ዲሲፕሊንና በረከቱ




መንፈሳዊ ዲሲፕሊንና በረከቱ


ጽሁፌ የሚያተኩረው ምሳ 2፡1-2 ላይ ሲሆን እናንተ ጊዜ ሲኖራችሁ ሙሉ ምእራፉን በቂ ጊዜ ሰጥታችሁ አጥኑት፡፡በዚህ ምእራፍ ላይ ምሳ 2፡6 እንደ መግቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ቃሉ አንዲህ ይነበባል፡-‹‹እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ››ይህ ቃል ሎጎስ ስለሆነው የእግዚአብሄር ቃል ወይም መጽሀፍ ቅዱስን ስናነብ በቀጥታ ስለምናገኘው አእምሮአዊ መረዳት ሳይሆን ከእግዚአብሄር መንፈስ በቀጥታ ስለምንቀበለው መረዳትና ማስተዋል ነው የሚናገረው፡፡ከዚህ ቃል ጋር ኢሳ 55፡10-11 ተመሳሳይነት አለውና ያንቡት፡፡እጅግ መልካም የሆነ የተስፋ ቃል ነው ነገር ግን መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው ጥበብንና ማስተዋልን የምንቀበለው የሚለውን ነው፡፡ለኔ መንገዶቹ በጥቅሉ ሶስት ይመስሉኛል፡-
  • ከቃሉ ጋር ጠበቅ ያለ ህብረትና ግንኙነት ሲኖረን
  • የጌታን ፊት በጸሎት አጥብቀን ስንፈልግ
  • ቃሉን በህይወታችን በተግባር ስንፈጽም
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት መንገዶች በሚገባ ደጋግመን ስናደርግ መንፈሳዊ ማስተዋላችንና መረዳታችን እየጨመረ ስለሚሄድ ወደ ህይወታችን የሚመጣው እድገትና ለውጥ ቀላል አይሆንም፡፡
ምሳ 2፡1-4 ላይ ቃሉ በህይወታችን መውሰድ ስለሚገባን ወሳኝ እርምጃዎችና የምንከፍላቸውን ዋጋዎች ያሳየናል፡፡እነዚህንም በዝርዝር አሰቀምጫቸዋለሁ፡-
  • ቃሉን ብትቀበል
  • ጆሮህ ጥበብን ብታደምጥ
  • ልብህን ወደ ማስተዋል ብታዘነብል
  • በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት
  • ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት
  • ለማስተዋል ድምጽህን ብታነሳ
  • እንደ ብር ብትፈላልጋት
  • እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት
እነዚህ ከላ ያሉት ስምንት ትእዛዞች በሁለት ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡-
1ኛ፡-ከቃሉ ጋር የጠበቀ ቁርኝትና ጥናት
2ኛ፡-ከቃል ጥናቱ ጋር አብሮ የሚሄድ የጠበቀ ጸሎት
የእግዚአብሄር ቃል መርህ እንደሚያስተምረን ፡-ትእዛዝ -----------------------------›በረከት
የእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝንና በረከትን አጣምሮ የያዘ ነው፤ስለዚህ ትእዛዞቹን ሳናደርግ የቃሉ በረከት ወደ ህይወታችን አይመጣም፡፡ከላይ ያሉትን ስምንት ተግባሮች በህይወታችን ስንለማመድ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን በረከቶች እንይ፡-
  • በዚያን ጊዜ እግዚአብሄርን መፍራት ታውቃለህ
  • የአምላክህን እውቀት ታገኛለህ/አምላክን በግል በሚገባ ታውቀዋለህ(በእንግሊዝኛው ‹‹you will gain knowledge of God>>)
  • መለኮታዊ ጥበቃው በህይወትህ ይበዛል
  • ነፍስህ በመንፈሳዊ ደስታ ትጥለቀለቃለች
  • ጽድቅንና ፍርድን መልካም መንገድን ታስተውላለህ (discernment)
  • በደጋግ ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ(success)
በተግባር ደረጃ የቃሉ ብርሀን በህይወታችን ሲበዛና እንደ ቃሉ ስንኖር ከሶስት ትልልቅ ጥፋቶች እንድናለን፡-
1ኛ፡-ከክፉ መንገድ  እናመልጣለን  (ወደ ስድስት ጥፋቶች ከቁጥር 12 እስከ 15 ተዘርዝረዋል)
2ኛ፡-በቀጥታ ከዝሙት (sexual sins) እና ከሚያመጣብን ጥፋት እንድናለን
3ኛ፡-ክፉ ከሆነውና ወደ ጥፋት ከሚወስደው የአለም አሰራር እናመልጣለን
ስለዚህ ለቃሉ ያልተከፋፈለ ልብን እንስጥ፤ፊቱን ሳናሰልስ እንፈልግ፤አድርጉ የሚለንም ለማድረግ እንጨክን !




Wednesday, August 28, 2013

የእግዚአብሄር ጉብኝት(spiritual visitation)



የእግዚአብሄር ጉብኝት(spiritual visitation)

<<Revival >> ወይም ‹‹መነቃቃት›› ማለት የሞተን ነገር ወደ ህይወት መመለስ ማለት ነው፡፡በሌላ በኩል ደግሞ መነቃቃት ማለት ባጭሩ ‹‹እግዚአብሄር መጣ››ማለት ነው፡፡ትንቢተ እንባቆ33 ላይ‹‹ እግዚአብሄር ከቴማን ቅዱሱም ከፋራን ይመጣል ›› ብሎ በወደፊት ጊዜ ግስ ነው የሚገልጸው፡፡በእንግሊዝኛ መጽሀፍ ቅዱሶች ውስጥ ግን “God came…” ብሎ በሀላፊ ጊዜ ነው አረፍተ ነገሩ የሚጀምረው፡፡እንባቆ ምእራፍ ሶስት ላይ ያለውን ቃል በመነቃቃት ዙሪያ የሚጽፉ የእግዚአብሄር ሰዎች ያዘወትሩታል፡፡እዚሁ ምእራፍ ላይ ከቁጥር 4 ጀምሮ ‹‹እግዚአብሄር ሲመጣ›› የሚሆኑ ድንቅ ክስተቶችን እስከ ቁጥር 16 ድረስ በስፋት ይዘረዝራል፡፡እኔ ግን አለፍ አለፍ እያልኩ በግልጽ በሚገባ ሁኔታ የተገለጹትን ለማስቀመጥ ልሞክር -  

  • ቆመ ምድርንም አወካት፤ተመለከተ አህዛብን አናወጠ፤የዘላለም ተራሮች ተቀጠቀጡ፤የዘላለም ኮረብቶች ቀለጡ
  • በቃልህ እንደማልህ መቅሰፍትን አወጣህ ቀስትንም ገተርህ ምድርንም ሰንጥቀህ ፈሳሾችን አወጣህ
  • ተራሮች አንተን አይተው ተጨነቁ
  • ፍላጾችህ ከወጡበት ብርሀን የተነሳ ከሚንቦገቦገውም ከጦርህ ጸዳል የተነሳ ጸሀይና ጨረቃ በመኖሪያቸው ቆሙ
  •   በምድር  ላይ በመአትህ ተራመድህ አህዛብን በቁጣ አሄድሀቸው
  • የሀጢያተኛውን ቤት ራስ ቀጠቀጥህ መሰረቱን እስከ አንገቱ ገለጥህ
  •  የአለቆችን ራስ በገዛ በትራቸው ወጋህ
ከዚያም እንባቆ እግዚአብሄር እየመጣ እንደሆነ በመንፈሱ ስላወቀ እንዲህ ይላል፡-‹‹እኔ ሰምቻለሁ ልቤም ደነገጠብኝ ከድምጹ የተነሳ ከንፈሮቼ ተንቀጠቀጡ መንቀጥቀጥ ወደ አጥንቶቼ ውስጥ ገባ በስፍራዬ ሆኜ ተናወጥሁ››፡፡እግዚአብሄር በክብሩ በሰዎች መሀል ሲገኝ ብዙ ነውጥ እንደሚሆን ከላይ ጀምሮ ያሉት አገላለጾች ያሳዩናል፡፡የእግዚአብሄር መንፈስ በሀይል ወርዶብኝ ከንፈሬ በሀይል ተንቀጥቅጦና መናገር አቅቶኝ ያውቃል አንድ ጊዜ ብቻ ሳይሆን በርከት ያሉ ጊዜያት፡፡ለአገልግሎት መድረክ ላይ ወጥቼ ለተወሰነ ደቂቃ መስበክ እና ቃል ማውጣት አቅቶኝ ያውቃል፡፡ስለዚህ ይህ አገላለጽ በመጠኑም ቢሆን ይገባኛል፡፡
መዝ 61-35 ላይም እግዚአብሄር ሲነሳ ወይም ሲከሰት የሚሆኑ ድንቅ ነገሮች በስፋት ተዘርዝረዋል፡፡ይህ ክፍል ሲጀምር ‹‹እግዚአብሄር ይነሳ›› ብሎ ነው የሚጀምረው፡፡እግዚአብሄር ሲነሳ እና በክብሩ ሲገለጥ የሚታዩ ነገሮችን አለፍ አለፍ ብዬ እዘረዝራሉ፡- 

  •  ጠላቶቹ መግቢያ ነው የሚያጡት፡-ሰም በእሳት እንደሚቀልጥ ይቀልጣሉ፤ጢስ እንደሚበንን ይበናሉ
  • ጻድቃን በእርሱ ፊት ሀሴት ያደርጋሉ በሀይልም ደስ ይላቸዋል
  •  እስረኞች ከእስራታቸው ይፈታሉ
  • ምድር ትናወጣለች ሰማያት ያንጠባጥባሉ(የቃሉንና የመንፈሱ በህዝብ መሀል መዝነብን ነው የሚያሳየን)
  • የደከሙ ይበረታሉ ይጸናሉ
  • የጠፋው ቃል ይገኛል(እግዚአብሄር ቃሉን ይሰጣል) ብሎም እንቆቅልሽ ይፈታል
  • በቤት የምትኖር ምንም ተሳትፎ ያልነበራት ሴት እንኳን ምርኮ ተካፈለች ይላል(የበረከቱን ሰፊነት ነው የሚያመለክተን)
  • ብዙ ሰዎች መንፈሳዊ ስጦታዎችን ይቀበላሉ(የጸጋ ስጦታዎችን)
  • ብዙ ሰዎች ከብዙ ጉድ ይድናሉ ይወጣሉም(ከሞት መውጣትም በእግዚአብሄር ነው የሚለው ይህንን ያመለክታል)
  • ሀይል ያለው ቃል ይለቀቃል
  • ብዙ ሰዎች ሀይልንና ብርታትን ይቀበላሉ
እዚህ ላይ ትልቅ ሊስተዋል የሚገባው ነገር የእግዚአብሄርን በጉባኤና በህዝብ መካከል መገለጥ ሰው ሊያቅደውና ሊያደራጀው አይችልም፡፡ሁለት ነገሮች ለዚህ ክስተት ወሳኝ ናቸው -
1.የእግዚአብሄር ሉአላዊነት(God’s sovereignity):-ጌታችን ይህንን አይነት ክስተት ነፍሱ በወደደች ሰአት ያደርጋል
2.የሰው ሀላፊነት(man’s responsibility):-ሰው ይህ ክስተት መቼ እንደሚመጣ ባያውቅም በብዙ ናፍቆትና በጋለ ጸሎት መጠበቅ አለበት
የእግዚአብሄር ጉብኝት ወደ እኛ እንዲመጣ ልንኮተኩታቸው የሚገቡ ነገሮች የሚከተሉት ናቸው፡-
1.ከልብ የሆነና እውነተኛ መመለስ ያስፈልገናል (2 ዜና 713-15 ያንቡ)- ይህንን ቃል አንድ የእግዚአብሄር ሰው እንዲህ ብለውታል፡-
‹‹the final and finished formula for revival>>
2.መንፈሳዊ ጥማትና ረሀብ (ሉቃ 20-21)-አንድ ሰው በመነቃቃት ዙሪያ የጻፉት ጽሁፍ ላይ የማልረሳው ድንቅ ሁለት ነገሮች በልቤ ተጽፈው ቀርተዋል፡፡እነርሱም በእንግሊዝኛ <<fasting and feasting››  ሲሆኑ መጾምና የእግዚአብሄርን ቃል በብዛት መመገብ መንፈሳዊ ጥማትንና ረሀብን ያቀጣጥላሉ ብለው ነው ጽሁፉ ላይ የሚያስገነዝቡት፡፡በግሌ የመንፈስ ረሀቤ ሲቀንስ እነዚህን ሁለት ነገሮች አብዝቼ አደርጋለሁ፡፡
ዊሊያም ቡዝ የሚባሉ ትልቅ የእግዚአብሄር ሰው አንድ የቤተ ክርስትያን አገልጋይ በቤተ ክርስትያኑ ለውጥ አጥቶ ሲያማክራቸው እንዲህ አሉት፡‹‹try tears›› በአማርኛ ‹‹እስቲ እንባን ሞክር››ነው ያሉት፡፡ይህ አባባል ብዙ በጌታ ፊት መጮህ እንዳለብን ይጠቁመናል፡፡መዝ 142 ላይ ‹‹የሚያስተውል እግዚአብሄርን የሚፈልግ እንዳለ ያይ ዘንድ እግዚአብሄር ከሰማይ የሰው ልጆችን ተመለከተ››እንደሚል  የክብር ጌታ አይቶ እንዲራራ ለዚህ ለከበረ ነገር ዋጋ የሚከፍሉ ብርቱ የሆኑና የጸሎት ሚስጥር የገባቸው ሰዎች በዚህ ዘመን በጣም ያስፈልጋሉ፡፡
3›የተሰበረ ልብና መንፈስ(ኢሳ 5714-15)-እግዚአብሄር የልብ መሰበርንና ትህትናን ስለሚወድ በፊቱ ባዶነታችንና ያለሱ ምንም ማድረግ የማንችል መሆናችንን እውቅና በመስጠት  ውስጣችንን ማሳየት መቻል አለብን፡፡መዝ 34፡18 ላይ ‹‹ልባቸው ለተሰበረ እግዚአብሄር ቅርብ ነው›› ስለሚል የልብ መሰበር በህይወታችን እንዲመጣ በፊቱ መውደቅ አለብን፡፡
      


የእግዚአብሄር ጉብኝት ሲመጣ የሚታዩ ለውጦች - 

  •  ሀይል ይጨምራል
  • / ትጠራለች
  • ቅድስና የህይወት መሰረት ይሆናል
  • ንጹህ መለኮታዊ ፍቅር በመካከላችን መታየት ይጀምራል
  • / በውጭው አለም ማህበራዊ ተጽእኖን ማምጣት ትጀምራለች
ስለዚህ የእግዚአብሄር ጉብኝትና መልካሚቱ እጁ በትውልዳችን መሀል መጥታ ክብሩን እንድናይ ያለማሰለስና ያለመታከት እንጸልይ!