Wednesday, August 21, 2013

ህዝቤ ሰምቶኝ ቢሆን


ህዝቤ ሰምቶኝ ቢሆን


የጌታን ድምጽ ሰምቶ መራመድ ስኬታማ እንደሚያደርግ ምንም ጥርጥር የለውም፡፡የጌታን ድምጽ ደግሞ በተለያዩ መንገዶች እንሰማለን፡፡ለምሳሌ፡-
·       ቃሉን ስናነብ
·       ስንጸልይ
·       ከነቢያት፣ከአስተማሪዎች እና ከሰባኪዎች
·       በህልም ወዘተ
በህይወታችን የጌታ ምሪት እንዲበዛ ከእርሱ ጋር ያለን ህብረት እያደገና እየጠለቀ መምጣት አለበት፡፡ለዚህ ስኬት ደግሞ በእግሩ ስር እንደ ማርያም መገኘት ምርጫ ያለው ጉዳይ አይደለም፡፡መዝ 8113-16 የጌታን ድምጽ ሰምቶ ስለመራመድና በመንገዱ መሄድ ስላለው በረከትና ጥቅም ዘርዘር ተደርጎ ተቀምጧል፡፡ይህ ክፍል ያስደንቀኛል፡፡ከዚህ ቃል አንጻር ህይወቴን ሳየው እጅግ ያሳዝነኛል፡፡የእግዚአብሄር ቃል ትእዛዝ አለው ደግሞ በመታዘዝ ቃሉን ስንተገብር የሚመጣ በረከት አለ፡፡
ትእዛዝ------------------------›በረከት (ትልቅ መርህ)
ከላይ የጠቀስኩት ቃል ላይ ትእዛዞቹ ሁለት ናቸው፡-
·       ህዝቤ ሰምቶኝ ቢሆን
·       እስራኤል በመንገዴ ሄደው ቢሆን
በረከቶቹን በእራሴ እይታ ጠቅለል አድርጌ በሶስት አስቀምጫቸዋለሁ፡-
1.የጠላቶቻችን መሸነፍና መዋረድ
2.የረጅም ዘመን መንፈሳዊና አካላዊ ጤንነት
3.ከጌታ ጋር ከሚኖረን ህብረት የምናገኘው ከአእምሮ የሚያልፍ ጉብኝት(ከአለቱ ማር መጥገባችንና ከስንዴው ስብ መብላታችን የሚለው ሀሳብ ይህንን ያሳያል)
ይሄ ቃል ልካችን ነው፡፡ወደዚህ ቃል ልክ ለማደግና ድምጹን በመስማት የሚገኘውን በረከት ለመካፈል ደግሞ
·       ቃሉን መብላት ማሰላሰል እናም ባልተከፋፈለ ልብ ማጥናት ያስፈልገናል
·       ጠበቅ ያሉ መንፈሳዊ ጸሎቶችን ማድረግ ይጠበቅብናል
·       ጾምን መለማመድ በጣም ጠቃሚ ነው
እንዲህ ሶስቱን ያለማቋረጥ ብንተገብር እርግጠኛ ነኝ ህይወታችን ካሰብነው በላይ ይባረካል ያድጋልም፡፡
ጸሎት -ጌታ ሆይ ድምጽህን ሰምተን እንድንራመድ እርዳን!

ደራሲው

ገና ከጧቱ ገና ከህጻንነት
የተፈጸመውን እያንዳንዱን
              ክስተት
ያውቀዋል ደራሲው……
የምንጓዘውን
ሸካራ አቀበቱን
ለስላሳ መጥፎውን
ከሱ የተሰወረ የድርሰት ምእራፍ
የለንም በፊቱ የሱን ጥበብ የሚያልፍ
የተደረሰውን ድርሰቱን ስናየው
ዛሬ ላይ ቆመን ሁሉን ስናጤነው
ውብ አድርጎ እንዲሰራ ነገርን በጊዜው
እሱን ነው ያወቅነው
እሱን ነው የተማርነው
ተውኔቶች እኛ ነን
ደራሲው እሱ ነው ጽሁፉ ህይወታችን
ጠቅላዩ እሱ ነው በጁ ናት ነፍሳችን!

መዝ 139 ሙሉውን ምእራፍ በጸሎት መንፈስ ሆነው

እንዲያነቡትና እንዲያሰላስሉት ጋብዤዎታለሁ፡፡










No comments:

Post a Comment