Wednesday, August 21, 2013

ስውር እጅ

ስውር እጅ

የመከራ እሳት
የተግዳሮት ብዛት
የስብራት መአት
ተፈራርቆ ባይነት
ዛሬስ አበቃ ስል
አሁን አለፍኩ ስል
አየሁ ሲግተለተል
ልክ እንደ ኮክቴይል  
ድንገት ስል ጨረስኩኝ
ሌላ እየቀደመኝ
ተፈራርቆ እያሸኝ
እያንገደገደኝ
የምወድቅ መስሎኝ
ስንቱን ክፉ አሳየኝ
ግን ምህረት በዛና
ዛሬን አየሁና
በሀይል ተገርምኩኝ
ልቤም በምስጋና
ወርዶ ሰገደና
ሳመ ስውር እጁን
ያዳኝ የንጉሱን!


 

 

No comments:

Post a Comment