መንፈሳዊ ዲሲፕሊንና በረከቱ
ጽሁፌ የሚያተኩረው ምሳ 2፡1-2 ላይ ሲሆን እናንተ ጊዜ ሲኖራችሁ ሙሉ ምእራፉን በቂ ጊዜ ሰጥታችሁ አጥኑት፡፡በዚህ
ምእራፍ ላይ ምሳ 2፡6 እንደ መግቢያ ሆኖ ሊያገለግል ይችላል ብዬ አስባለሁ፡፡ቃሉ አንዲህ ይነበባል፡-‹‹እግዚአብሄር ጥበብን ይሰጣልና
ከአፉም እውቀትና ማስተዋል ይወጣሉ››ይህ ቃል ሎጎስ ስለሆነው የእግዚአብሄር ቃል ወይም መጽሀፍ ቅዱስን ስናነብ በቀጥታ ስለምናገኘው
አእምሮአዊ መረዳት ሳይሆን ከእግዚአብሄር መንፈስ በቀጥታ ስለምንቀበለው መረዳትና ማስተዋል ነው የሚናገረው፡፡ከዚህ ቃል ጋር ኢሳ
55፡10-11 ተመሳሳይነት አለውና ያንቡት፡፡እጅግ መልካም የሆነ የተስፋ ቃል ነው ነገር ግን መጠየቅ ያለብን እንዴት ነው ጥበብንና ማስተዋልን የምንቀበለው የሚለውን ነው፡፡ለኔ መንገዶቹ
በጥቅሉ ሶስት ይመስሉኛል፡-
- ከቃሉ ጋር ጠበቅ ያለ ህብረትና ግንኙነት ሲኖረን
- የጌታን ፊት በጸሎት አጥብቀን ስንፈልግ
- ቃሉን በህይወታችን በተግባር ስንፈጽም
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን
ሶስት መንገዶች በሚገባ ደጋግመን ስናደርግ መንፈሳዊ ማስተዋላችንና መረዳታችን እየጨመረ ስለሚሄድ ወደ ህይወታችን የሚመጣው እድገትና
ለውጥ ቀላል አይሆንም፡፡
ምሳ 2፡1-4 ላይ
ቃሉ በህይወታችን መውሰድ ስለሚገባን ወሳኝ እርምጃዎችና የምንከፍላቸውን ዋጋዎች ያሳየናል፡፡እነዚህንም በዝርዝር አሰቀምጫቸዋለሁ፡-
- ቃሉን ብትቀበል
- ጆሮህ ጥበብን ብታደምጥ
- ልብህን ወደ ማስተዋል ብታዘነብል
- በአንተ ዘንድ ሸሽገህ ብትይዛት
- ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት
- ለማስተዋል ድምጽህን ብታነሳ
- እንደ ብር ብትፈላልጋት
- እንደ ተቀበረ ገንዘብ ብትሻት
እነዚህ ከላ ያሉት
ስምንት ትእዛዞች በሁለት ሊጠቃለሉ ይችላሉ፡-
1ኛ፡-ከቃሉ ጋር የጠበቀ
ቁርኝትና ጥናት
2ኛ፡-ከቃል ጥናቱ
ጋር አብሮ የሚሄድ የጠበቀ ጸሎት
የእግዚአብሄር ቃል
መርህ እንደሚያስተምረን ፡-ትእዛዝ -----------------------------›በረከት
የእግዚአብሄር ቃል
ትእዛዝንና በረከትን አጣምሮ የያዘ ነው፤ስለዚህ ትእዛዞቹን ሳናደርግ የቃሉ በረከት ወደ ህይወታችን አይመጣም፡፡ከላይ ያሉትን ስምንት
ተግባሮች በህይወታችን ስንለማመድ ወደ ህይወታችን የሚመጡትን በረከቶች እንይ፡-
- በዚያን ጊዜ እግዚአብሄርን መፍራት ታውቃለህ
- የአምላክህን እውቀት ታገኛለህ/አምላክን በግል በሚገባ ታውቀዋለህ(በእንግሊዝኛው ‹‹you will gain knowledge of God>>)
- መለኮታዊ ጥበቃው በህይወትህ ይበዛል
- ነፍስህ በመንፈሳዊ ደስታ ትጥለቀለቃለች
- ጽድቅንና ፍርድን መልካም መንገድን ታስተውላለህ (discernment)
- በደጋግ ሰዎች መንገድ ትሄዳለህ(success)
በተግባር ደረጃ የቃሉ
ብርሀን በህይወታችን ሲበዛና እንደ ቃሉ ስንኖር ከሶስት ትልልቅ ጥፋቶች እንድናለን፡-
1ኛ፡-ከክፉ መንገድ
እናመልጣለን (ወደ ስድስት ጥፋቶች ከቁጥር 12 እስከ 15 ተዘርዝረዋል)
2ኛ፡-በቀጥታ ከዝሙት
(sexual sins) እና ከሚያመጣብን ጥፋት እንድናለን
3ኛ፡-ክፉ ከሆነውና
ወደ ጥፋት ከሚወስደው የአለም አሰራር እናመልጣለን
ስለዚህ ለቃሉ ያልተከፋፈለ
ልብን እንስጥ፤ፊቱን ሳናሰልስ እንፈልግ፤አድርጉ የሚለንም ለማድረግ እንጨክን !
No comments:
Post a Comment