ከልብህ ኀዘንን አርቅ
ወደ ስምንት አመት ገደማ ይሆናል፡፡በአንድ ከፍ ያለ የልብ ስብራት ውስጥ ሆኜ መቆዘም አብዝቼ ነበር፡፡ኀዘኔ ከበድ ያለ ስለነበር ከሰው ጋር መገናኘትና ማውራት አስጠልቶኝ ሁሉ ነበር፡፡በዛ ሁኔታ ውስጥ ሳለሁ የጌታ መንፈስ ደረሰልኝና አንድ ነገር አበራልኝ፡፡እርሱም ይህንን ያለሁበትን ሁኔታ የማራገፍ ኀላፊነት የኔ እንደሆነ በቃሉ ብርሃን ተገነዝብኩ፡፡ ውስጤን የለወጠው ቃል የሚገኘው መክብብ ላይ ሲሆን እንዲህ ይላል፡-
“ከልብህ ኀዘንን አርቅ”(መክብብ 11:10)
ይህ ቃል የበራልኝ ቀን በሚገርም ሁኔታ ነበር ውስጤ በግርምት የተሞላው፡፡አዝኜ የሰይጣንና የአጋንንቱ መጫወቻ ሆኜ እያላዘንሁ መቀመጥ እንደሌለብኝ በሚገባ ገባኝ፡፡ጌታ ከዛም ከነበርሁበት ሁኔታ ለመውጣት ጠንከር ያሉ ጸሎቶችን በመያዝ ትግል መጀመር እንዳለብኝ አመለከተኝ፡፡
ባጋጣሚ የምኖርበት ቤት አጠገብ አንድ የመሠረተ ክርስቶስ አጥቢያ ቤ/ክ ነበርና እዚያ በፈረቃ ግቢውን የሚጠብቁትን ሠራተኞች እያስፈቀድሁ ለረጅም ሰዓታት ባዶ አዳራሽ ውስጥ መጮኽ ጀመርሁ፡፡መጀመሪያ ይህንን ትግል ስጀምር ልክ ግምብ የመግፋት ያህል ይሰማኝ ነበር፡፡የሚሰማኝ ስሜት ሳይበግረኝ በጸሎት መገሥገሥ ጀመርሁ፡፡በመሀል በመሀል አንዳንዴ ካለሁበት ሁኔታ ጋር የሚዛመድ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎችን እያጠናሁና እያሰላሰልሁ ከዚያ ደግሞ ቀጥዬ በመቃተትና የጌታ መንፈስ እንዲረዳኝ በመማጸን ሳልፈወስ ከምሽጌ ላልወጣ ለራሴ ቃል ገባሁ፡፡
ለተወሰኑ ቀናት እንዲህ ባለ ሁኔታ ካሳለፍኩ በኋላ ሁኔታው ሁሉ ተገልብጦ ሰላምና ደስታ በማያቋርጥ ሁኔታ በልቤ ውስጥ ይፈስ ጀመር፡፡ዝማሬ፣ አምልኮ፣ስግደት ፣ውዳሴ ወዘተ በሕይወቴ ተትረፈረፈ፡፡እየጸለይኩ ውዬ፤ስለጌታ አውርቼ ፤አመስግኜ ወዘተ አልረካም ነበር፡፡እዚህ ምድር ላይ ሁሉ የምኖር አልመስለኝ ሁሉ አለ፡፡የእግዚአብሔር ህልውና በሚገርም ሁኔታ እላዬ ላይ ነበር፡፡ብቻዬን ሆኜ ማንም ሳያወራኝ ሁሉ ሳቅ ያስፈነድቀኝ እንደነበር ሁሉ ትዝ ይለኛል፡፡የነበርኩበትን ሁኔታ በቃላት መግለጽ ያዳግተኛል፡፡ወገኖቼ ልብ በሉ እያጋነንሁ አይደለም እውነተኛ ነገር ነው የምናገረው፡፡ክርስትና ዝም ብሎ ስርአት እንዳልሆነ በሕይወቴ አይቻለሁ፡፡
“እግዚአብሔርም የተቤዣቸው ይመለሳሉ እየዘመሩም ወደ ጽዮን ይመጣሉ የዘላለም ደስታ በራሳቸው ላይ ይሆናል ሐሤትንና ደስታን ያገኛሉ ኀዘንና ትካዜም ይሸሻሉ” (ኢሳ 35፡10) ብሎ የሚለው ቃል ምን ማለት እንደ ሆነ በጥቂቱም ቢሆን ይገባኛል::አዎ ያ ሁሉ ኀዘንና ትካዜ የት አንደገባ እስገሚገርመኝ ድረስ በሐሤት ተጥለቀለቅሁ፡፡ለዚህ ነው ቃሉ “በዚያም ቀን ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ይወርዳል ቀንበሩም ከውፍረት የተነሳ ይሰበራል”(ኢሳ 10፡27) የሚለው፡፡ማለትም ጠበቅ ያሉ ጸሎቶችን ስናዘወትር የጌታ መንፈስ በውስጣችን እየጨመረ ስለሚሄድ ማንኛውንም አዚም ለመስበር የምንችልበትን አቅምና ጉልበት እናገኛለን፡፡
በጽኑነት ከልብ ሆነንና በቀጣይነት ሳንታክት በምንጸልየው ጸሎት ብዙ ድንቅ መለኮታዊ ነገሮችን እናያለን የሚል መረዳት አለኝ ፡፡ስለዚህ ከነካ ነካ የጸሎት ሕይወት ጌታ ወደ ጠለቀ ልምምድ እንዲከተን ሳንታክት ፊቱን እንሻ፡፡እንዲህ ብናደርግ ያስደንቀናል፡፡ስሙ ለዘላለም የተባረከ ይሁን!

No comments:
Post a Comment