Sunday, September 1, 2013

የጽድቅ ውሳኔና በረከት




የጽድቅ ውሳኔና በረከት





ይህ ጽሁፍ የሚያተኩረው ዳን 1፡1-10 ላይ ነው፡፡
መግቢያ ነጥቦች ፡-
  • እስራኤላውያን በባቢሎናውያን መማረክና መወሰድ
        ------->የእግዚአብሄር ፈቃድ ነበረ(ኤር 27፡6)
  • የዳንኤል የጽድቅ ውሳኔ “እንዳይረክስ በልቡ አሰበ”
        -------->ይህ ውሳኔ እጅግ ጠቃሚ ውሳኔና የዳንኤል የስኬት ምንጭ ነበር
ዳንኤል እንዳይረክስ በልቡ ያሰበው ፡-
  • የብሉይ ኪዳንን ህግጋት ጠንቅቆ ያውቅ ስለነበረ ነው
  • ለጣኦት የተሰዋ ምግብ እንደሚያረክሰው ስለሚያውቅ ነበር
  • ለጣኦት የተሰዋን ምግብ መብላቱ ቃል ኪዳኑን መስበር እንደሆነም ስላሰበ ነበር
  • ይህንን ውሳኔ ደግሞ በእግዚአብሄር ጸጋና ረድኤት አደረገው
ዳንኤል እና ጓደኞቹ በባቢሎን ነበሩ ነገር ግን የባቢሎን አልነበሩም፡፡ውስጣዊ ለውጥ (inner conviction) ውጫዊ ጫናን ያሸንፋልና ነው፡፡ጉልህ የሚታዩ ትምህርታዊ ነጥቦች፡-
  • የእግዚአብሄር ሉአላዊነት በዚህ ክፍል ውስጥ በሚገባ ታይቷል
  • የእግዚአብሄር በፈተና ውስጥ ያለው አቅርቦት እና ረድኤት በሚገባ ተስተውሏል
  • የዳንኤል ዲሲፕሊን ፡‹‹አሰበ›› በእንግሊዝኛው ‹‹he purposed in his heart>> ማለትም የምናስበው ነገር የምናደርገውንና ምርጫችንን እንደሚወስን ያስገነዝበናል
  • ዳንኤል ክፉውንና መልካሙን የመለየት ችሎታ(discernment) ነበረው
  • ዳንኤል ጽናት ነበረው፡-ዋናው ቁም ነገር መጀመራችን ሳይሆን መጨረሳችን ነው
ከተወሰዱት እርምጃዎች የተነሳ የታዩት አዎንታዊ ለውጦች፡-
  • ዳንኤል በባቢሎን ኢምፓየር ከፍ አለ
  • ትልልቅ አስደናቂ ትንቢቶችን ተቀበለ
  • እየሱስ ያጸደቀው ነቢይ ሆነ ማቴ 24፡15
  • ከእነ ኖህና እዮብ ጋር ሁሉ ተቆጠረ  እዝ 14፡14
  • ጓደኞቹ በየአውራጃው ላይ ተሾሙ ዳን 2:49
ነገር ግን ሊታወቅ የሚገባው ነገር የዚህ ሁሉ ክስተት ባለቤት ደራሲ እግዚአብሄር ነበረ፡፡በእኛም ህይወት ደራሲው እሱ ነው፡-
  • እግዚአብሄር እራሱ አሳልፎ ሰጣቸው ዳን 1፡2
  • እግዚአብሄር እራሱ በባለስልጣኞቹ ፊት ሞገስን ሰጣቸው
  • እግዚአብሄር ጥበብን፤ችሎታንና ማስተዋልን ሰጣቸው ዳን 1፡17
ስለዚህ በአለም ምናምንቴ ነገር እንዳንረክስ፤በእግዚአብሄርም በሰውም ፊት ሞገስ እንድናገኝና ጥሩ የህይወት ምስክርነት እንዲኖረን ሶስት ነገሮችን እናድርግ ፡-
  • ባላጋራችን ዲያቢሎስ የሚውጠውን ፈልጎ(ሊያረክሰን) እንደሚያገሳ አንበሳ በዙሪያችን ይዞራልና ጸንተን እንቃወመው
  • ይህንን አለም እንዳንመስልና እንዳንወሰድ በልባችን መታደስ እንለወጥ ፡-ቃሉን እናጥና፣እናሰላስል፣እናስብ
  • በዙሪያችን ብዙ የሚያረክሱ ነገሮች አሉና እንንቃ ብሎም ጨክነን እምቢ እንበል፡-በዚህ ዙሪያ ጸጋ እንዲበዛልን ጠንከር ያሉ ጸሎቶችን እንጸልይ
እነዚህን ከላይ የተጠቀሱትን ሶስት እርምጃዎች ብንተገብር በሰዎች ላይ ልዩ የህይወት ተጽእኖና ምስክርነት ይኖረናል፡፡እግዚአብሄር ሆይ እርዳን!

No comments:

Post a Comment