ቅዱስ አለመርካት(Holy Dissatisfaction)
ቅዱስ
አለመርካት(Holy Dissatisfaction)ማለት በቀጥታ ሲተረጎም ያለንበት የቅድስና፣የመለየት እና ከጌታ ጋር ያለን ሕብረት ደረጃ ስለማያረካን የምናደርገው እየጨመረ የሚሄድ ትጋትና መሰጠት ነው፡፡በሌላ አገላለጽ እየጨመረ የሚሄድ ጤናማ የሆነ መንፈሳዊ ቅናትና ፍለጋ ነው፡፡በዚህ ዓይነት ግሥገሣ ወደ መንፈሳዊው ዓለም እየጠለቀ የሚሄድ ሕይወት ደግሞ ብዙ ርካታና ዕረፍት ይኖረዋል፡፡በመንፈሳዊ ሕይወታችን ብዙ ትጋት በጨመርን ቁጥር ብዙ መንፈሳዊ በረከቶች መለቀቅ ይጀምራሉ፤የእግዚአብሔር ጸጋ እየጨመረ ስለሚመጣ ለብዙ ቀጣይ ፍለጋ እንጠናከራለን፡፡በዚህ ሂደት ጸንተን ስንቀጥል፣የሚገርም ኡደት(cycle of pursuit) ውስጥ እራሳችንን እናገኘዋለን፡፡በተግባር ደረጃ ቅዱስ አለመርካት ማለት አንብበን የማንጠግብበት፤የእግዚአብሔርን ቃል ሰምተን የማንረካበት፤ጸልየን በቃ የማንልበት እየጨመረ የሚሄድ የተቀጣጠለ(vibrant) ሕይወት ነው፤መጸለይ
እንጂ
አለመጸለይ የማንችልበት! ማንበብ እንጂ አለማንበብ የማንችልበት! ቃሉን በራብ፣በጉጉትና
በጥማት መስማት እንጂ
አለመስማት የማንችልበት!
ነቢዩ ኤርምያስ ባንድ በኩል እዚህ ኡደት (cycle of pursuit) ውስጥ ስለገባ ይመስለኛል“አታለልከኝ”(ኤርምያስ
20፡7) ብሎ የተናገረው፤እግዚአብሔር እያታለለ መውጣት ወደ ማይችልበት ጥልቅ መንፈሳዊ ሕይወት ውስጥ ሲከተው(የኔ መረዳት ነው)፡፡እንዲህ
ዓይነት ግሥገሣ፣ትጋትና ቅናት ማብቂያ የለውም ወደ ሥጋዊ ነገሮች ተመልሰን መንፈስን እስካላጠፋን በስተቀር፡፡ይህንን
ሐሳብ የሚጠቁሙ ተመሳሳይ ክፍሎችን እነሆ፡-
1. “እስከ እግዚአብሔር
ፍጹም
ሙላት
ትሞሉ
ዘንድ….”
(ኤፌሶን 3፡19)
2. “በመንፈስ የምትቃጠሉ ሁኑ” (ሮሜ 12፡11)
3. “መንፈስ ይሙላባችሁ እንጂ በወይን ጠጅ አትስከሩ(በነገራችን ላይ መጠጥም ባይሆን ብዙ የሚያሰክር ነገር አለ) ይህ ማባከን ነውና”(ኤፌ 5፡16-20)
4. “አጵሎስ የዮሐንስን ጥምቀት ብቻ አውቆ በመንፈስ ሲቃጠል” ( ሐዋ. ሥራ 18፡25)
ልባችን ሙሉ በሙሉ ጌታ ላይ ሆኖ በዚህ አይነት ቅናትና ፍለጋ (passion and craving) ስንቀጥል፣ጌታን በሚገባ እያወቅነውና ልባችን በመንፈሳዊ መረዳት እየተለወጠ ይመጣል፡፡ስለዚህም እውነተኛ የሆነ መንፈሳዊ ደስታ እና ዕረፍት ወደ ሕይወታችን ይመጣል(1ጴጥ 1፡7-9)::ከዚህ የተነሣ በሕይወታችን አላስፈላጊ የሆኑ እና መንገድ የሚዘጉ ነገሮችን የመጣል አቅም እናገኛለን፡፡በጥቅሉ መሰጠታችን
ስለሚጨምር፣የእግዚአብሔር መንግስት ሐሳብ ሙሉ በሙሉ ይወርሰናል፡፡እዚህ
መንፈሳዊ ሂደት ውስጥ ያለ ሰው ቅዱስ አለመርካት (Holy Dissatisfaction) ውስጥ ገብቷል ማለት ይቻላል፡፡
ወደ
እዚህ
ወደ
ተባረከ ሕይወት ለመግባት የሚያስፈልገን ነገር ሁሉ ተሰጥቶናል(1ጴጥ 1፡3)፡፡አሁን የእኛ ድርሻ ይህንን በውስጣችን የታመቀ ኃይል በሚገባ እንዲለቀቅ ማቀጣጠል ነው ፡፡የእግዚአብሔር
ቃል “ከሰል ፍምን እንጨት እሳትን ያበዛል”
(ምሳሌ 26፡21) እንደሚል ብዙ ማገዶ(የእግዚአብሔር ቃል) ወደ ውስጣችን መክተት ያስፈልገናል፡፡በተገኘው ጊዜ ሁሉ የእግዚአብሔርን ፊት መፈለግም ወሳኝ ነው፡፡ከጸሎታችን ጋር ጾም አብሮ ቢጣመር እጅግ አስደናቂ ነገሮችን እናይበታለን(ኢሳይያስ 58) ብዬ አምናለሁ፡፡
ሐዋርያው ጳውሎስ እዚህ ቅዱስ አለመርካት ውስጥ ስለነበር ነው እንዲህ ብሎ የተናገረው፡-
“አሁን እንዳገኘሁ ወይም አሁን ፍጹም እንደ ሆንሁ አይደለም ነገር ግን ስለ እርሱ በክርስቶስ ኢየሱስ የተያዝሁበትን ያን ደግሞ እይዛለሁ ብዬ እፈጥናለሁ፡፡ወንድሞች ሆይ እኔ ገና እንዳልያዝሁት እቆጥራለሁ ነገር ግን አንድ ነገር አደርጋለሁ በኋላዬ ያለውን እየረሳሁ በፊቴ ያለውን ለመያዝ እዘረጋለሁ በክርስቶስ ኢየሱስ ከፍ ከፍ ያለውን የእግዚአብሄርን መጥራት ዋጋ እንዳገኝ ምልክትን እፈጥናለሁ፡፡እንግዲህ ፍጹማን የሆንን ሁላችን ይህን እናስብ….” (ፊሊጵስዩስ 3፡12-15)
ይህ
ቃል
ቅዱስ
አለመርካትን የሚያመጡ ሁለት መተግበር ያለባቸውን ነገሮችን ያሳየናል፡፡እነርሱም እነዚህ ናቸው፡-
1.በኋላ ያለውን መርሳት:-
ያለፉ ጥፋቶች፣ውድቀቶች፣ስኬቶች
እና ድሎች ወደ ፊት እንዳንዘረጋ ሊያደርጉን ወይም ሊጐትቱን ይችላሉና!
2.በፊታችን ያለውን ለመያዝ መዘርጋት፡-በፊታችን
ተዝቆ
የማያልቅ ብዙ መንፈሳዊ ምስጢርና በረከት አለ፤ጌታ ዓይናችንን ከፍቶ ያሳየን እንጂ!
ስለዚህ የእምነታችንን ጀማሪና ፈጻሚ እያየን ወደ ፊት በእምነት መቀጠልና መዘርጋት መደራደሪያ የማይሰጠው ርምጃ መሆኑ ሊታወቅ
ይገባል!
ስለዚህ ወገናቼ ማንኛውንም በኋላችን ያለውን
ሊጎትተን የሚታገለንን ነገር ሁሉ እየረሳንና እየጣልን ጌታ ያሰበልንን መንፈሳዊ በረከት ለመያዝ እንዘርጋ!
No comments:
Post a Comment